Hosea 11

የእግዚአብሔር ፍቅር ለእስራኤል

1“እስራኤል ገና ሕፃን ሳለ ወደድሁት፤
ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት።
2እስራኤል ግን አብዝቼ በጠራኋቸው
አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ቅጆች እንዲሁ ሲሆኑ፣ ዕብራይስጡ ግን በጠሯቸው ይላል።
ቍጥር፣
አብዝተው ከእኔ
ሰብዐ ሊቃናት እንዲሁ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን ከእነርሱ ይላል።
ራቁ፤
ለበኣል አማልክት ሠዉ፤
ለምስሎችም ዐጠኑ።
3ኤፍሬምን እጁን ይዤ፣
እንዲራመድ ያስተማርሁት እኔ ነበርሁ፤
ነገር ግን የፈወስኋቸው እኔ እንደ ሆንሁ፣
እነርሱ አላስተዋሉም።
4በሰው የርኅራኄ ገመድ፣
በፍቅርም ሰንሰለት ሳብኋቸው፤
ቀንበሩን ከጫንቃቸው ላይ አነሣሁላቸው፤
ዝቅ ብዬም መገብኋቸው።

5“ታዲያ ንስሓ መግባትን እንቢ በማለታቸው፣
ወደ ግብፅ አይመለሱምን?
አሦርስ አይገዛቸውምን?
6በከተሞቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዛል፤
የበሮቻቸውን መወርወሪያ ይቈርጣል፤
ስለ ክፉ ዕቅዳቸውም ይደመስሳቸዋል።
7ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ማለትን መረጡ፤
ወደ ልዑል ቢጣሩም፣
በምንም ዐይነት አያከብራቸውም።

8“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ?
እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ?
እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ?
እንዴትስ እንደ ሲባዮ እፈጽምብሃለሁ?
ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤
ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቷል።
9የቍጣዬን መቅሠፍት አላመጣም፤
ተመልሼም ኤፍሬምን አላጠፋም፤
እኔ በመካከላችሁ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ እንጂ፣
ሰው አይደለሁምና፣
በቍጣ አልመጣም።
ወይም በማንኛውም ከተማ ላይ በተቃውሞ አልመጣም

10 እግዚአብሔርን ይከተላሉ፤
እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤
እርሱ ሲያገሣ፣
ልጆቹ እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ።
11እንደ ወፍ ከግብፅ፣
እንደ ርግብ ከአሦር፣
እየበረሩ ይመጣሉ፤
እኔም በቤታቸው አኖራቸዋለሁ”
ይላል እግዚአብሔር

የእስራኤል ኀጢአት

12ኤፍሬም በሐሰት፣
የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፤
ይሁዳ ለአምላክ የማይገዛ፣
የታመነውን ቅዱሱን የሚቃወም ነው።
Copyright information for AmhNASV